የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የሕክምና ግብዓቶች ቆጠራን በሁሉም ማዕከላዊ መጋዘኖችና ቅርንጫፎች ማከናወን ጀምሯል።
የመጋዘን እና የፍሰት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ጀማል እንደገለጹት፤ ወደ ቆጠራው ከመገባቱ በፊት የሰው ኃይል የማሟላት፣ ለቅርንጫፎች የሚላኩ ግብዓቶችን ቀድሞ የመላክ እና መጋዘኖችን ለቆጠራ ምቹ የማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በስፋት ተከናውኗል ብለዋል።
ቆጠራው ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ከጥር 29 እስከ የካቲት 01 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዶ መላው ሠራተኛ በከፍተኛ ተነሳሽነት እየሠራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
የዘንድሮውን የግማሽ ዓመት ቆጠራ ለየት የሚያደርገው የግብዓቶች የመጠን ልኬት (Volumetric measurement) ታሳቢ ተደርጎ እየተከናወነ መሆኑ ነው።
በመጨረሻም ቆጠራው መሰረታዊ መርሆችን ተከትሎ እንዲከናወንና የተገኙ መረጃዎች በጥንቃቄ ወደ ሲስተም እንዲገቡ አቶ መሀመድ አሳስበዋል።
#ማገልገል_ክብር_ነው!
ሠላም ይደግ