የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት በውቢቷ ጅማ ከተማ ባዘጋጀው የስድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠለሞን ንጉሴ፤ የዜጎችን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመድኃኒት አቅርቦት ሥርዓቱ ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ ሊመራ እንደሚገባ አሳሰቡ።
አቶ ሠለሞን በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጥራታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶችን ባልተቆራረጠ መልኩ ለህብረተሰቡ ለማድረስ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
✅ ዘመናዊ የአቅርቦት ሥርዓት፦ የመድኃኒት አቅርቦት ፍላጎትን መሠረት ያደረገ እንዲሆን ለማስቻል የተደረጉ ማሻሻያዎችና አገልግሎት አሰጣጡን ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ተቃኝተዋል።
📈 የቅድሚያ ውል የተገባለት የአቅርቦት ስርዓቱ (Committed Demand and supply system_CDSS)ትግበራ፦ በበጀት ዓመቱ የተጀመረው የቅድሚያ ውል የተገባለት የአቅርቦት ሥርዓት ያለበት ደረጃ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ለጤና መድህን አገልግሎቱ ያመጣው ትልቅ እመርታ ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።
🤝 የጋራ ቅንጅት፦ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱን ማጠናከር ለጤና አገልግሎቱ ስኬት "የማዕዘን ድንጋይ" መሆኑን በመገንዘብ፣ በቀጣይም በቅንጅት ለመሥራት ከመግባባት ላይ ተደርሷል።
ለጤና መድህን አገልግሎት መጠናከርና ለዜጎች ተጠቃሚነት ትኩረት በመስጠት ለተከናወኑ ተግባራት አቶ ሠለሞን ንጉሴ ለኢጤመአ አመራርና ለተሳታፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የመድረኩም ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አሰራሩን በቴክኖሎጂ ታግዞ በመድኃኒት አቅርቦት ላይ እያመጣ ያለውን ለውጥ አድንቀዋል ።
#ማገልገል ክብር ነው!