የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ የደንበኞች ቀን መከበሩ የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ በቀጥታ ከተገልጋዮች ጋር በመወያየትና በመመካከር የደንበኞችን ፍላጎት ለማሣካት የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአገልግሎቱ ማርኬቲንግ እና የደንበኞች እይታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ገዳምነሽ በበኩላቸው፣ የደንበኞች ቀን መከበር ከአገልግሎቱ እና ከደንበኞች በጋራ የሚጠበቁብንን ኃላፊነቶች ለመወያየትና በአጠቃላይ የጤና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እንደሚያግዝ ገልፀዋል።
በእለቱ ከደንበኞቻችን ጋር በተቋሙ አጠቃላይ አሠራሮች፣ ውል የተገባለት አቅርቦት /CDSS/ ያመጣቸውን ለውጦችና በቀጣይ መሻሻል እና በጋራ መሠራት ያለባቸውን ስራዎች ውይይይት ተካሂዷል፡፡
በመጨረሻም አገልግሎቱ የህክምና ግብዓቶች የመገኘት ምጣኔን ለማሻሻል፣ ደህንነቱንና ጥራቱን የጠበቀ ግብዓት ለማቅረብ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲደርስ ለማድረግ እንዲሁም ለደንበኞች የተሻለ የአቅርቦት ሰንሰለት ለመፍጠር በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
# ማገልገል ክብር ነው!
በማህሌት አበራ