የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦትን ለማሳለጥ የተዘረጋው አዲሱ ሥርዓት አፈጻጸም ተገመገመ።
News
February 21, 2026
46 views

የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦትን ለማሳለጥ የተዘረጋው አዲሱ ሥርዓት አፈጻጸም ተገመገመ።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) አዲሱን አዋጅ ተከትሎ ወደ ትግበራ የገባውን "ውል የተገባለት የአቅርቦት ሥርዓት" (Committed Demand & Supply System_CDSS) አፈጻጸም ከቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆችና ከዳይሬክተሮች ጋር በጋራ ገመገመ።

በግምገማው ወቅት የሦስቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች የገለጹዋቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

🔹 አቶ ታሪኩ በላቸው፦ "የሕክምና ግብዓት አቅርቦት መቆራረጥን በዘላቂነት ለመፍታት ይህ ሥርዓት በ2018 ዓ.ም የጀመርነው ቁልፍ ስራችን ነው፤ በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ያሉ ሁሉም አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው።"

🔹 አቶ አቅናው ካውዛ፦ "በዚህ ዓመት የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦት ምጣኔ ትልቅ መሻሻል አሳይቷል። ሥርዓቱ በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ የመረጃ ግልጸኝነት (Transparency) እንዲሰፍን ከፍተኛ እገዛ አድርጓል።"

🔹 አቶ ሰለሞን ንጉሴ፦ "ሥርዓቱ በአገልግሎቱ እና በጤና ተቋማት መካከል ያለውን የመድኃኒት መገኘት ምጣኔ (Availability) ተቀራራቢ እንዲሆን አድርጎታል። በቀጣይም ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን የዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።"

የሥርዓቱ (CDSS) ዋና ዋና ጥቅሞች፦
✅ የአቅርቦት መቆራረጥን በዘላቂነት መፍታቱ፤
✅ በየደረጃው ያሉ አካላትን ተጠያቂነትና የሥራ ድርሻ በዝርዝር ማስቀመጡ፤
✅ የቅርንጫፎችን ብቃት ለመመዘን የሚያስችል ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያ (KPI) መዘጋጀቱ።

✅ በውል ተዋዋዮች መካከል እኩል ተጠያቁነት የሚያሠፍን መሆኑ
✅ አስገዳጅ በሆነ የህግ ማእቀፍ ውስጥ መተግበሩ

አገልግሎቱ በቀጣይም የጤና ተቋማት የሚፈልጉትን ግብዓት በወቅቱና በጥራት እንዲያገኙ በትኩረት እንደሚሠራ አረጋግጧል።

#ማገልገል_ክብር_ነው! 🇪🇹
#EPSS
ማህሌት አበራ
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service