የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 8ውን የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ "የባለድርሻ አካላት ትብብርና ቅንጅት ለመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ውጤታማነት እና ፈጣን ምላሽ ሰጭነት በሚል መሪ ቃል በአርባምንጭ ከተማ ከመጋቢት 18-20/2018ዓ.ም እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የጤና ሚኒስቴር ድኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ፣ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር እና የቦርድ አባል ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ፣ የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አጋር ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የሀገራችንን የጤና ተደራሽነት ለማረጋገጥ፣ የዜጎቻችንን ሕይወት ለመታደግና የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለታችንን ይበልጥ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና የማይበገር ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት ለማደስ መድረኩ ወሳኝ ሚና አለው ሲሉ ወ/ሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል።
አክለውም ባለፉት ሰባት ዓመታት በዚህ መድረክ ስናካሂድ የቆየነው ውይይት በዘርፉ ላይ የአሰራር ማነቆዎችን በመፍታት በርካታ ተጨባጭ ለውጦችን አምጥቷል ብለዋል።
አሁን ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ የአቅርቦት ሰንሰለቱ ፈተና ላይ ቢገኝም የባለድርሻ አካላት ትብብር በማጠናከር ማለፍ እንችላለን ሲሉ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ተናግረዋል።
ባለድርሻ አካላት ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ስጋትን በመቀነስ ያላቸው ሚና እንዲሁም የአገልግሎቱ ዋና ዋና ማሻሻያዎች እና በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ የተገኙ ስኬቶች አጠቃላይ እይታ በዝርዝር ቀርቧል።
መድረኩ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎቻች የሚፀናበት እና ለቀጣዩ ጉዞ ከወትሮ በተለየ መልኩ አዲስ አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሚሆን ይጠበቃል።
#ማገልገል_ክብር_ነው
ሰላም ይደግ