Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
አገልግሎቱ 19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
October 13, 2026
161 views

አገልግሎቱ 19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሠንደቅ ዓላማ የሀገር ክብር፣ የሉዓላዊነትና የጋራ ታሪክ ምልክት በመሆኑ ዜጎች ልዩነቶቻቸውን በማክበር ለጋራ ዓላማ በአንድነት እንዲቆሙ የሚያስታውስ ብሔራዊ መገለጫ መሆኑን አቶ አቅናው ካውዛ ተናግረዋል።

በዓድዋ ድል የተመሰከረው የኢትዮጵያውያን የጋራ ተጋድሎ የሀገር ነፃነትና ክብር በአንድነት በመቆም እንደሚጠበቅ የሚያሳይ ታሪካዊ ትምህርት መሆኑን በመጥቀስ፣ የዚህን ታሪክ ትሩፋት ወደ ሰላም፣ ልማት፣ ተቋማዊ ብቃትና የሕዝብ የኑሮ መሻሻል መቀየር የዘመኑ ትውልድ ኃላፊነት መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።

አገልግሎቱ ይህንን ብሔራዊ ኃላፊነት በተግባር ለመወጣት መድኃኒቶችንና የሕክምና ግብዓቶችን በጥራት፣ በተመጣጣኝ ዋጋና በዘላቂነት ለጤና ተቋማት ማቅረብ ላይ እንደሚሠራ ምላሽ የሰጡት ምላክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ይህም የሕዝብን ጤና ከመጠበቅ ባለፈ የጤና ሥርዓቱን ለማጠናከርና ለሀገር ዘላቂ ልማት አስተዋጽኦ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

በመጨረሻም የአገልግሎቱ ሠራተኞች ለተቋሙ ተልዕኮ በቁርጠኝነት እንዲሠሩ፣ የትብብር መንፈሳቸውን እንዲያጠናክሩና ለሕዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት በቀጣይነት እንዲያሻሽሉ ጥሪ አቅርበዋል፤ የሠንደቅ ዓላማችን ክብር የሚጠበቀው በጋራ ኃላፊነት፣ መከባበርና ለጋራ ዓላማ በመሥራት መሆኑንም ገልፀዋል።

#ማገልገል ክብር ነው!
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service