አክለውም ኢትዮጵያ ጉባኤውን በማስተናገዷ እና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በዝግጅቱ ሂደት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ፕሮፌሰር ራቪ አገልግሎቱ ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፍ የጤና አቅርቦት ሰንሰለት ልህቀት ረገድ ላሳየው አመርቂ አፈጻጸም እውቅና ማግኘቱን በማስታወስ፣ ተሳታፊዎች በተቋሙ የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ባደረጉት ጉብኝት የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችን መመልከት መቻላቸውን ጠቁመዋል።
በጉባኤው የተሳተፉ እንግዶች በበኩላቸው፤ መድረኩ ከተለያዩ አገራትና ተቋማት ከመጡ ባለድርሻ አካላት ጋር አዳዲስ የትብብርና የሙያዊ ግንኙነት ዕድሎችን እንደፈጠረላቸው ገልጸው፣ አገልግሎቱ ላደረገላቸው መልካም አቀባበልና አስተናጋጅነት አመስግነዋል።
ጉባኤው በዓለም አቀፍ የጤና አቅርቦት ሰንሰለት ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት፣ የተቋማትን ትብብር ለማጠናከርና የጤና ግብዓቶችን ተደራሽነት ለማሻሻል ጠቃሚ የልምድ ልውውጥ መድረክ ሆኖ ተጠናቋል።
#ማገልገል_ክብር_ነው