Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
30 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
17 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 48 days ago
View All
በጤና አቅርቦት ሰንሰለት ተግዳሮቶችና በመንግሥት ድጋፍ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
November 23, 2026
2 views

በጤና አቅርቦት ሰንሰለት ተግዳሮቶችና በመንግሥት ድጋፍ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ዶ/ር አብዱልቃድር በውይይቱ ላይ እንዳስረዱት፣ አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ለሀገር ውስጥ የመድኃኒት አምራቾች ለዘርፉ የሠጠውን መልካም እድል፣ የማኅበረሰብ ጤና መድን አገልግሎት 68 ሚሊዮን ሕዝብን መድረሱ የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓት ፍላጎትን በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጓል ብለዋል። ይህንን ፍላጎት በተሟላና ቀጣይነት ባለው መንገድ ለማሟላትም መንግሥት ለዜጎች ክብር እና ተጠቃሚነት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

አገልግሎቱ በዲጂታል ሥርዓት በመታገዝ ከግዥ ጀምሮ እስከ ጤና ተቋማት ድረስ የሚደርሱ የእያንዳንዱን ትዕዛዝ ሂደቶች በአንድ ማያ ገጽ መከታተል እንደቻለ ያብራሩት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የግዥ ሂደቶችን ለማፋጠን የሚያግዙ አዋጅና መመሪያዎች በፓርላማ መጽደቃቸውንም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በጤና ተቋማት የሚታየውን ደካማ የፍላጎት ትንበያ፣ የፋይናንስ ክፍተትና የክፍያ መዘግየት ለመቅረፍ ውል የተገባለት የአቅርቦት ሥርዓት (CDSS) ወደ ትግበራ መግባቱን አንስተዋል። ይህም በተረጋገጠ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የአቅርቦት ዕቅድና ግዥ ለማከናወን እንዳስቻለ አስረድተዋል።

የሕዝብን ፍላጎት ወደ ተግባራዊ ለውጥ መቀየር፣ የሕግ ተጠያቂነትን ማጠናከርና የጤና ተቋማትን ፍላጎት በትክክል መለየት ለተሻለ የጤና አቅርቦት ሰንሰለት ወሳኝ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

የፓናል ውይይቱ ሀገራት ያላቸውን ልምድ እንዲጋሩ፣ የጋራ ተግዳሮቶችን እንዲለዩ እንዲሁም በመንግሥት ድጋፍ፣ በተቋማት ትብብርና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ ያለመ ነው።

#ማገልገል_ክብር_ነው
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service