Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
35 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
22 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 43 days ago
View All
19ኛው የዓለም የጤና አቅርቦት ሰንሰለት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል  ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
November 18, 2026
21 views

19ኛው የዓለም የጤና አቅርቦት ሰንሰለት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንደገለጹት፣ አፍሪካ ከዓለም አቀፉ የበሽታ ሸክም ሩቡን ያህል በአህጉሪቱ የሚከሰት ቢሆንም ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ መድኃኒቶቿንና ከ99 በመቶ በላይ ክትባቶቿን ከአህጉሪቱ ውጭ ታስገባለች ብለው ፤ ይህንን ጥገኝነት ለመቀነስ የሕክምና ግብዓቶችን የማምረት አቅም ማሳደግና የጋራ መፍትሔዎችን መፈለግ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዣን ካሴያ በበኩላቸው፣ አፍሪካ ለሕዝቦቿ የሚያስፈልጉ የጤና ግብዓቶችን በራሷ ለማምረት ማቀድና በትጋት መሥራት እንዳለባት ገልጸዋል።

አክለውም የጤና ዘርፉ ውጤታማነት ከአጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር በቀጥታ የተያያዘ በመሆኑ አህጉሪቱ በትብብር መሥራት እንደሚገባትም አሳስበዋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በበኩላቸው የጤና ግብዓት አቅርቦት ውጤታማነት መለካት ያለበት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ እናቶችና ሕፃናት የሚፈልጉትን የጤና ግብዓት በወቅቱ ማግኘታቸውን በማየት መሆን እንዳለበት ተናግረው ፤ የጤና ግብዓቶችን በጋራ የመግዛትና የማደራረስ ሥርዓት (Pull Procurement) በማጠናከር በትብብር መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ጉባኤው በቀጣይ ቀናት በፖሊሲ፣ በገበያ፣ በካፒታልና በጤና ግብዓቶች ተደራሽነት ላይ በመወያየት ለዘላቂና ውጤታማ የጤና አቅርቦት ሰንሰለት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን እንደሚያመላክት ይጠበቃል።

#ማገልገል_ክብር_ነው
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service