Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
35 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
22 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 43 days ago
View All
የአፍሪካ የሕክምና ግብዓት ማምረቻ ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች አገልግሎቱን ጎበኙ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
November 18, 2026
17 views

የአፍሪካ የሕክምና ግብዓት ማምረቻ ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች አገልግሎቱን ጎበኙ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ በጉብኝቱ ወቅት የአገልግሎቱን የሥራ አደረጃጀት፣ የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ግዥ፣ ማከማቻና ሥርጭት ሂደቶች፣ እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ የአሠራር ሥርዓቶችን ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል።

አገልግሎቱ በመድኃኒት አቅርቦት ዘርፍ ያካበተውን ልምድና ተሞክሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ማካፈል፣ በአህጉሪቱ የጤና ግብዓቶች አቅርቦት ሥርዓትን ለማጠናከርና በሀገራት መካከል ትብብርን ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ዘርፍ እውቅና ያላቸው ባለሙያው ዶ/ር ኢያን ባርተን፣ የአገልግሎቱ የግዥ ሂደት በጠንካራ አቅም እየተመራ መሆኑን ጠቁመው ፤ የቀድሞው የግዥ ስትራቴጂ ተሻሽሎ ትኩረቱን በሀገር ውስጥ ምርት ልማት ላይ ማድረጉም የሚደነቅ እመርታ መሆኑን አስረድተዋል።

ሌላዋ ጎብኚ ክርስቲን ኦዮ በበኩላቸው፣ የአገልግሎቱን የሥራ አደረጃጀት፣ የዳሽቦርድ አጠቃቀም፣ የግዥ ሂደት ግልጽነትና የደህንነት ሥርዓት አድንቀው ፤ የመጋዘን ክምችት አስተዳደር፣ የፍላጎት ትንበያ ሂደትና የአመራር አሠራር ዘዴዎችም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ክርስቲን ኦዮ አክለውም፣ አገልግሎቱ ያስመዘገበው ስኬት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አርአያ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው፣ የአህጉሪቱ የመድኃኒት አቅርቦት ተቋማት የአገልግሎቱን ተሞክሮ ለመቀመርና ልምድ ለመለዋወጥ ተቋሙን መጎብኘት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

#ማገልገል_ክብር_ነው
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service