በተጨማሪም የቀጥታ ስርጭት ምጣኔ፣ ውል የተገባለት የአቅርቦት ሥርዓት አፈጻጸም፣ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በተደረገ የልምድ ልውውጥ የተገኙ ውጤቶች፣ የሀገር ውስጥ አምራቾች የሕክምና ግብዓት አቅርቦት ዕድገትና የተቋማዊ ፖሊሲ ማሻሻያ ሥራዎችን በዝርዝር አስረድተዋል።
በውይይቱ ላይ በተሳታፊዎች በኩል ስለ ሕክምና ተቋማት የግብዓት ፍላጎት አሰራር፣ የተቀናጀ የመረጃ ሥርዓት (ERP) አጠቃቀም እና የሎጂስቲክስ ቁጥጥር ሥርዓት ዙሪያ ጥያቄዎች ተነስተው በአቶ ሰለሞን ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
በመጨረሻ ተሳታፊዎቹ የአገልግሎቱን የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦት፣ ማከማቻና ስርጭት ሥርዓት እንዲሁም የኔትወርክ መቆጣጠሪያ ክፍሎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
#ማገልገል_ክብር_ነው!