Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
3ኛው የአፍሪካ የሕክምና ግብዓት ማምረቻ ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንስ መካሄድ ጀመረ    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
October 29, 2026
116 views

3ኛው የአፍሪካ የሕክምና ግብዓት ማምረቻ ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንስ መካሄድ ጀመረ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ከጥቅምት 16 እስከ 19 ቀን 2019 ዓ.ም. በሚካሄደው በዚህ መድረክ የአፍሪካ የጤናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት፣ አምራቾች፣ ዓለም አቀፍ አጋሮችና ባለሀብቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር መሉቀን አርጋው እንደተናገሩት ኤግዚቢሽኑ የገበያ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እንደሚያግዝ ገልፀው ፤ ኢትዮጵያም የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለመደገፍና አዳዲስ ባለሀብቶችን ለመሳብ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እያስፋፋች መሆኗን አመልክተዋል።

አገልግሎቱም ከሀገር ውስጥ አምራቾች ጋር ውሎችን በመፈጸምና የገበያ ዕድልን በማረጋገጥ የአገር ውስጥ ምርትን እያበረታታ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች አምራቾች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሰ ተፈሪ በበኩላቸው፣ መድረኩ የኢትዮጵያን የማምረት አቅምና በፖሊሲ ዘርፍ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ለአፍሪካና ለዓለም ለማስተዋወቅ፣ እንዲሁም አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

በኤግዚቢሽኑ ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃን የጠበቁ የሕክምና ግብዓቶችን ለማምረት የሚያግዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና የምርምር ውጤቶች የቀረቡ ሲሆን ፤ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትም በመድረኩ ላይ የተቋሙን ሥራዎችና ለሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት ያለውን ድጋፍ እያስተዋወቀ ይገኛል።

#ማገልገል_ክብር_ነው!
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service