Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
30 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
17 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 48 days ago
View All
የሌጎስ ዩኒቨርሲቲ የአቅርቦት ሰንሰለት ፕሮፌሰሮች አገልግሎቱን ጎበኙ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
November 23, 2026
1 views

የሌጎስ ዩኒቨርሲቲ የአቅርቦት ሰንሰለት ፕሮፌሰሮች አገልግሎቱን ጎበኙ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በተለይም አገልግሎቱ የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦትን የበለጠ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ተደራሽ ለማድረግ እየተገበራቸው ያሉ ስትራቴጂዎችን፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን፣ የመጋዘን አስተዳደርንና የአቅርቦት ሰንሰለት ቁጥጥር ሥርዓቶችን አብራርተዋል።

አገልግሎቱ በተቀናጀ የአሠራር ሥርዓት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሰው ኃይል ልማት ላይ በማተኮር የአቅርቦት ሰንሰለቱን ይበልጥ ውጤታማና ዘላቂ ለማድረግ፣ እንዲሁም ለጤና ተቋማት የሚደርሰውን የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦት ለማሻሻል እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ፕሮፌሰሮቹ በበኩላቸው በጉብኝቱ የተመለከቷቸውን የተቋሙ የአሠራር ሥርዓቶችና የአቅርቦት ሰንሰለት አመራር ልምዶች አድንቀው፣ ከጉብኝቱ ጠቃሚ ልምዶችን ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

#ማገልገል_ክብር_ነው
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service