የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም. ማንሰራራት ቀንን አስመልክቶ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለሚገኙ ታካሚዎች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የEPSS የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምፀሐይ ዳታ ተገኝተው የማዕድ ማጋራት ተግባሩ በጤና ተቋሙ ህክምናቸውን ለሚከታተሉ ታካሚዎች የድጋፍ፣ የአብሮነትና የተስፋ መልዕክት ለማስተላለፍ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም፣ የማንሰራራት ቀን መርሃ ግብሮች የማህበረሰብ ተሳትፎን፣ የአብሮነት መንፈስንና የሰው ለሰው ድጋፍን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል።
የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩም ታካሚዎችን በመደገፍና በማበረታታት ማህበራዊ ኃላፊነትን በተግባር የሚያሳይ በጎ ተግባር ሆኖ ተከናውኗል።
ማገልገል ክብር ነው