ስልጠናው በአዲስ አበባ ሳሬም ሆቴል የተካሄደ ሲሆን፣ ከዋናው መ/ቤትና ቅርንጫፎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች በSEAH ክስተቶችን መለየትና መከላከል፣ ፈጣንና ተገቢ ምላሽ መስጠት፣ የጉዳይ ሪፖርትና የምርመራ ሂደት፣ የSurvivor መብትና ደህንነት፣ ሚስጥራዊ የሪፖርት መስመር እንዲሁም የCase Management Support አሰራር ላይ ግንዛቤና ክህሎት አግኝተዋል።
የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ዳታ በማጠቃለያ መልዕክታቸው፣ ስልጠናው በዋናው መ/ቤትና ቅርንጫፎች የSEAH ግንዛቤን ለማስፋት፣ ተጠያቂነትና አክብሮት የሰፈነበት የሥራ አካባቢ ለመፍጠር እና የጉዳይ አስተዳደርና ምላሽ አሰጣጥን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
ወ/ሮ ዓለምፀሐይ አክለውም፣ የሰልጣኞች ቀጣይ ኃላፊነት ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተቋሙ በማስፋፋት የSEAH መከላከልን፣ የሠዎችን መብትና ደህንነት ማስቀደምን እና በተቋሙ ውስጥ ትክክለኛ መርህን ማጠናከር መሆኑን አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም፣ የAIHA ሲኒየር ፕሮግራም ማናጀር ወ/ሮ ሳባ ስንታየሁ፣ የSEAH መከላከያ ደንቦችን ተግባራዊ ማድረግና ግልጽ፣ አስተማማኝና ሚስጥራዊ የጥቆማ እና የጉዳይ አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ደህንነቱ የተጠበቀ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ወ/ሮ አለም ፀሐይ ሠራተኞች ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ሪፖርት ማድረጊያ ስርአት መዘጋጀቱን ገልፀው በhttp://172.16.250.15:8080/help/woman.php በመግባት ቅሬታቸውንና ያጋጠማቸውን ችግር ሪፖርት እንዲያደርጉ ጠቁመዋል፡፡
ማገልገል ክብር ነው!