Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
በ2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብአት ምርት ኤግዚቢሽን አምራቾች ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሄደ
News
April 04, 2026
302 views

በ2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብአት ምርት ኤግዚቢሽን አምራቾች ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሄደ

2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን እና 10ኛው የኢትዮ ሄሌዝ ኤግዚቢሽን "ጤናችን በምርታችን"በሚል መሪ ቃል በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል ከመጋቢት 24-26/2018 እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህም የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ጨምሮ የፋይናንስ ፣ የኢንቨስትመንት እና የሚመለከታቸው ተቋማት የተሳተፉበት የሀገር ውስጥ ምርት ለማሳደግ በተሰጡ እድሎች እንዲሁም በሚገጥሙ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንደገለፁት ለሀገር ውስጥ አመራቾች አስተማማኝ ገበያ በመፍጠር ትልቅ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አንስተው ፤ የፋይናንስ ተቋማት ለመድኃኒት ዘርፉ የቅድሚያ ቅድሚያ በመሰጠት አጋርነታቸውን ሊያሳዩ ይገባል ብለዋል።

በተለይም የማክሮ ኢኮኖሚ መሻሻል ለህክምና ግብአት ምርት የተለየ ትኩረት እንዲሰጠው እንዳስቻለ የፋይናንስ ተቋማት የተናገሩ ሲሆን ድጋፋን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለሀገር ውሰጥ ምርት ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ በመፍጠር ላይ እንደምትገኝ በውይይቱ ተነስቷል።

በፓናሉ ማጠቃለያ የአገልግሎቱ ማኔጅመንት አባላት ኤግዚቢሽኑን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

#ማገልገል_ክብር_ነው
ሰላም ይደግ
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service