መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የግሎባል ፈንድ አባላት የአገልግሎቱን ዋና መስሪያ ቤት መጋዘኖች የጎበኙ ሲሆን፣ የአቅርቦት ስርዓቱ በዘመናዊ መንገድ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል።
ግሎባል ፈንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤና ስርዓቶችን ለማጠናከር በተለይም ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ ሳንባ ነቀርሳ፣ ወባ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር የሚሰራ ዓለም አቀፍ የልገሳ ድርጅት ነው።
የፈንዱ ከፍተኛ የፋይናንስ ሀላፊ (Chif Finance ) አዳ ፋዬ እና ከፍተኛ ፓርትፎሊዮ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ጆርጅ ሳክቫሪሌዝን ጨምሮ ሌሎች አባላት በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው የአገልግሎቱን ወቅታዊ ሁኔታ ገምግመዋል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንግዶቹን በደማቅ አቀባበል ተቀብለው፣ ተቋሙ በስትራቴጂክ እቅዱ መሰረት ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። እንዲሁም የሀገር ውስጥ አምራቾች ለ7 ዓመት የሚቆይ የገበያ ትስስር እንዲኖራቸው መደረጉን እና የመድኃኒት አቅርቦት በዘመናዊ የመረጃ ስርዓት ተደግፎ ግልፅነትንና ተደራሽነትን እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የግሎባል ፈንድ አባላት በበኩላቸው የተቋሙ የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት የጤና መድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱን በእጅጉ እንዳሻሻለ በመግለጽ እየታየ ያለውን እመርታ አድንቀዋል።
#ማገልገል_ክብር_ነዉ
ዘጋቢ፦ አማኑኤል ወርቃየሁ