ከደረጃ 7 በታች አነስተኛ ገቢ ላላቸው የአገልግሎቱ ሠራተኞች የሚደጎሙበት አሰራር የተዘረጋ መሆኑን እና ባዓላት ሲመጡ ባለን እርስ በርስ የመረዳዳት ኢትዮጵያዊ እሴት ማዕድ በማጋራት መጭውን በዓል ወገኖቻችን በደስታ እንዲያሳልፉ በማሰብ መርሃ ግብሩ መዘጋጀቱን የአገልግሎቱ የዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ገልጸዋል ።
የማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብሩ አገልግሎቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ትልቅ ተቋማዊ እሴት እንዳለው ማሳያ ነው ብለዋል።
ሰራተኞች በአሉን ምክንያት በማድረግ ለተደረገዉ ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
#ማገልገል_ክብር_ነው
ሰላም ይደግ