Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
የአቅርቦት ሰንሰለት ተፅዕኖን ለመቋቋም የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
News
April 14, 2026
302 views

የአቅርቦት ሰንሰለት ተፅዕኖን ለመቋቋም የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሕክምና ግብዓቶችን ለመንግሥት የጤና ተቋማት እንደሚያቀርብ ይታወቃል። በመሆኑም፣ የአቅርቦት ሰንሰለት ተፅዕኖ ስጋት አስተዳደር ዕቅድ በማዘጋጀት ከመላው ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል።

የተቋሙን የአቅርቦት ሰንሰለት ለማስቀጠል የተያዙ የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን ለአገልግሎቱ ሠራተኞች በዝርዝር ያቀረቡት የምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሰለሞን ንጉሴ ሲሆኑ፤ በውይይቱም በዘጠኝ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮሩ የአቅርቦት ሰንሰለት ስጋት አስተዳደር የማኔጅመንት ውሳኔዎችን አቅርበዋል።

ተግዳሮቶችን መሻገር እንደሚቻል ታሳቢ ተደርጎ፣ በዚህ ወቅት የሚወሰዱ ጥንቃቄዎችና እርምጃዎች እንደ ተቋምም ሆነ እንደ ሀገር ትልቅ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል ያሉት ደግሞ የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ በላቸው ናቸው። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የጤና ሥርዓት አገልግሎቱ እንዳይስተጓጎል ሁሉም በጋራና በርብርብ መስራት እንደሚገባው አሳስበዋል።

በመጨረሻም በተነሱ ሐሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

ማገልገል ክብር ነው!
ማኅሌት አበራ
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service