ተቋሙ በዓለም አቀፍ የቢዝነስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከፍተኛ ስም ካላቸው ሽልማቶች አንዱ የሆነውን Transformation Project of the Year Award" አሸናፊ መሆን የቻለው በ2024 በሁሉም ቅርንጫፎች ከአንድ ቋት የሚነሳ የቴክኖሎጂ አሰራር “Project SMILE” SAP S/4HANA የተሰኘውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ የተቀናጀ የዲጂታል ለውጥ ስራውን በስኬት በማጠናቀቁ ነው።
አገልግሎቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስራውን ከመጀመሩ በፊት ባካሄደው ጥናት፣ 60% የሚሆኑት የሥራ ሂደቶች በእጅ (manual) የሚከናወኑና ለብክነት የተጋለጡ እንደነበሩ ተለይቷል። በተጨማሪም 42% የሚሆኑት አሰራሮች ለተቋሙ ምንም አይነት ተጨማሪ እሴት የማይጨምሩ (non-value add) ሆነው ተገኝተዋል።
ይህንን ተግዳሮት ለመፍታት የተዘረጋው የዲጂታል አሰራር የሚከተሉትን ዋና ዋና ውጤቶችን አስመዝግቧል
- የመረጃ ማዕከልነት (Single Source of Truth): ፋይናንስ፣ ግዥ፣ ክምችት፣ መጋዘን እና የሰው ኃይል አስተዳደርን በአንድ ማዕከላዊ የSAP አሰራር ስርዓት በመተግበር የተቀናጀ የሪፖርት ሥርዓት ተዘርግቷል።
- የቅጽበት ክትትል (Real-time Tracking)፦ የመድኃኒት ስርጭትን መከታተል የሚያስችል አቅም መፈጠሩ።
- ግልጽነትና ተጠያቂነት:- የታመነ የግዥ ስርዓት መዘረጋት ፣ የሃብት ብክነትን በመቀነስ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱን ቀልጣፋና አስተማማኝ ደረጃ በማድረጉ ላይ ይገኛል ።
ይህ ታላቅ ዓለም አቀፍ እውቅና የጤና ሚኒስቴር አመራር ቁርጠኝነት፣ የተቋሙ መላው አመራር እና ሰራተኞች ጥረት እንዲሁም የዓለም አቀፍ አጋሮች ( The Global Fund፣ SEIDOR እና Deloitte Consulting) በተቀናጀ የአጋርነት እና የጋራ ትብብር ውጤት ነው።
ይህ ስኬት ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የጀመረችው የዲጂታይዜሽን ጉዞ ማሳያ ከመሆኑም ባለፈ፣ለሀገራችን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የጀርባ አጥንት ለሆነው 'Digital Ethiopia 2030' ስትራቴጂ የዲጂታል ልማት ግብ በተግባር ማሳያ ሆኖ ይቆጠራል ።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) ይህንን ሽልማት ማግኘቱ በአፍሪካ ቀዳሚና ዘመናዊ የመድኃኒት አቅርቦት ተቋም ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ ለማሳካት ተጨማሪ ጉልበት እንደሚሆነው እና በቀጣይነት ያለሁ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀና የተቀላጠፈ የጤና አገልግሎት ግብዓት አቅርቦት ስርዓቱን በመዘረጋት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ።