Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
አገልግሎቱ ከUSG SCS ፕሮጀክት በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ቴክኒካል ትብብር እና የአሰራር ድጋፍ ላይ ውይይት ተደረገ  ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
May 20, 2026
257 views

አገልግሎቱ ከUSG SCS ፕሮጀክት በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ቴክኒካል ትብብር እና የአሰራር ድጋፍ ላይ ውይይት ተደረገ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንዳሉት ጠንካራ ፣ ቀልጣፋ እና ቀጣይነት ያለው የጤና ግብዓት አቅርቦት ሰንሰለት ስርዓት ለመገንባት ጠንካራ ተቋማዊ አጋርነት ያለውን ጠቀሜታ አጽንኦት ሰጥተው ፤ በመላ ሀገሪቱ አስፈላጊ የሆኑ የጤና ግብዓቶች ያለማቋረጥ ተደራሽ ለማድረግ የተቀናጀ ርብርብ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

አቶ ኤድመአለም እጅጉ በትብብር ለመስራት የታቀዱ አካባቢዎችን ሰፋ ያለ መግለጫ ያቀረቡ ሲሆን ፤ ከቀረቡት አንኳር ጉዳዮች መካከል የ SCS ፕሮጀክትን ድጋፍ EPSS ቅድሚያ ከሚሰጣቸው እቅዶች ጋር መጣጣሙ ፣ ውጤታማ ትግበራና የሚለካ ውጤት ለማስመዝገብ ስትራቴጅካዊ ቁጥጥር መደረጉ ፣ የቴክኒክ ቅንጅት እና የአፈፃፀም ክትትልን የሚሸፍን የተዋቀረ የአስተዳደርና የቅንጅት ማዕቀፍም መዘጋጀቱ ፣ የሰው ሃይል ልማት ፣ እንዲሁም ERP ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ድጋፍ በሚደረግባቸው አንዳንድ የቴክኒክ ድጋፍ ዘርፎች ላይ ትኩረት የተሰጠባቸው ጉዳዮች ቀርበዋል ።

የአደጋ ጊዜ ምላሽ ስትራቴጂካዊ አስተዳደር ፣ አጋርነትና ቅንጅት የአቅርቦት ሰንሰለት ፣ ስጋት አስተዳደር እና ግብዐት የመገኘት ምጣኔ ፣ ስልታዊ ግዥ ትንበያ እና የተቀናጀ የብሔራዊ አቅርቦት እቅድ እና ተቋማዊ ብስለት በመጨመር የስርጭት ስርዓቶች እና የመጨረሻ ማይል አቅርቦት ማመቻቸት ቀዳሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተከናውኗል ።

የታቀዱት የድጋፍ ቦታዎች ከEPSS ስትራቴጂክ እቅድ ጋር ስላላቸው አግባብነት እና መጣጣም ያላቸውን አድናቆት ገልፀው ዶ/ር አብዱልቃድር ፤ ተቋማዊ ብስለትን እና የረዥም ጊዜ የስርአት አፈጻጸምን በሁሉም የስራ ደረጃዎች ለማስቀጠል የአቅርቦት ሰንሰለት የሰው ሃይል እና የአመራር ልማት ወሳኝ ምሰሶ መሆኑን አስምረውበታል።

የስብሰባው አላማ በEPSS እና በUSG SCS ፕሮጀክት መካከል ያለውን አጋርነት ለማረጋገጥ እንደ አስፈላጊ መድረክ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ አስፈላጊ የሆኑ የጤና ምርቶች ወጥነት ያለው አቅርቦት እንዲኖር ሁለቱም ወገኖች ቅንጅታዊ አሰራርን ፣ ተቋማዊ አቅምን እና የአሰራር ቅልጥፍናን በማጠናከር ላይ ገንቢ ውይይት አድርገዋል።

# ማገልገል ክብር ነው!
ማኅሌት አበራ
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service