Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
ጠንካራ አመራር ለህክምና ግብዓት አቅርቦት ስርዓት መዘመን ወሳኝ ነዉ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
May 20, 2026
300 views

ጠንካራ አመራር ለህክምና ግብዓት አቅርቦት ስርዓት መዘመን ወሳኝ ነዉ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨

“እምነት ሁሉን የሚለውጥ ቁልፍ ነገር ነው።” ያሉት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ፤ የአቅርቦት ስርዓቱ እንዲሳለጥ እዉነተኛ የተግባቦት ልምምድ ሊኖር ይገባል ብለዋል። ይህም ሊሰፍን የሚችለው እንዲህ ባለ ወቅታዊና በተግባር የተደገፈ የአመራር ስልጠና እንደሆነም ገልፀዋል።

በተጨማሪም ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት የአቅርቦት ሰንሰለት ስርዓት በቁርጠኛ አመራር ተደግፎ የተጠያቂነትና የግልፀኝነት ስርዓትን ማረጋገጥ መቻል እንደሚገባ አስረድተዋል።

አሰልጣኝ ሙሉጌታ አባተ እንዳሉት በሳይንሳዊ መንገድ የአመራሩን ክህሎት በማሳደግ ጥሩ የአቅርቦት ሰንሰለት እንዲኖር የሚያስችል የምክክር ጊዜ እንደነበረ ጠቁመዉ የመድኃኒት እጥረትን ለመቀነስ፣ የአቅርቦት መቋረጥን ለመከላከልና የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠናዉ በጤና አቅርቦት ሰንሰለት (Health Supply Chain) ውስጥ ጠንካራ “አመራርና አስተዳደር” ለመድኃኒቶች፣ ክትባቶች፣ የላብራቶሪ ግብዓቶችና ሌሎች የሕክምና ቁሳቁሶች በትክክል እንዲገዙ፣ እንዲከማቹ፣ እንዲሰራጩ እና ለተጠቃሚዎች በጊዜው እንዲደርሱ ፣ ፖሊሲዎችና የአስተዳደር ሂደቶች በአግባቡ እንዲተገበሩ ወሳኝ ነዉ ብለዋል።

ስልጠናው በዙር የሚቀጥል ሲሆን የመጀመሪያውን ዙር በስኬት ላጠናቀቁ የስራ መሪዎች ከዋና ዳይሬክተሩ እጅ የምስክር ወረቀት አግኝተዋል ።

#ማገልገል ክብር ነዉ
አማኑኤል ወርቃየሁ
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service