ድጋፍ የተደረጉ መሳሪያዎች የማህበረሰቡን የጤና ተደራሸነት ለማጎልበት እና በዘርፉ ህክምናን ለማስተማር የሚረዳ ነዉ ሲሉ ወ/ሮ ፍሬህይወት ተናግረዉ ፤ ማይክሮስኮፖቹ ለባህርዳር ፣ ጎንደር እና ሀረመያ ዩንቨርሲቲ ሆስፒታሎች ተደራሽ እንደሚደረጉ ጠቁመዋል፡፡
ባለፈዉ በጀት አመት 5 ኒዉሮሰርጂካል ማይክሮስኮፖችን ድጋፍ እንዳደረጉ የሪች አናዘር ፋዉንዴሽን አስተባባሪ ዶ/ር ያዕቆብ ሰመረ አስታዉሰዉ መሳሪያዎቹ ከ2000 በላይ ታካሚዎች ከሀገር ዉጭ ይታከሙ የነበሩትን በሀገር ዉስጥ አገልግሎት እንዲያገኙ አስችሏል ብለዋል፡፡
አገልግሎቱ መሳሪያዎችን የተመረጡ ቦታዎች ላይ በአግባቡ የማድረስ እንዲሁም አስፈላጊዉን ክትትል እና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ተናግረዉ ፤ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ