Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
ዶ/ር አቡባካር ካምፖ የዩኒሴፍ ተወካይ በኢትዮጵያ አገልግሎቱን ጎበኙ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
May 26, 2026
278 views

ዶ/ር አቡባካር ካምፖ የዩኒሴፍ ተወካይ በኢትዮጵያ አገልግሎቱን ጎበኙ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ዶ/ር አቡባካር ካምፖ እንዳሉት፤ የክትባት አያያዝ እና እስከ መጨረሻው ተጠቃሚ ድረስ የሚደረገው ስርጭት እጅግ አድናቆት የሚገባው መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማገዝ የተሰሩ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በቀጣይም ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት የማምረት አቅሟን ይበልጥ ለማሳደግ ጠንክራ መስራት እንደሚገባት አሳስበዋል።

የአቅርቦት ሰንሰለት መሠረተ ልማት፣ የጤና የሰው ኃይል አቅም፣ የሕክምና ግብዓት አቅርቦት፣ እስከ መጨረሻው ተጠቃሚ ድረስ ለማድረስ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ድጋፍ፣ የክትባት ደህንነት እና አቅም ማሳደግ እንዲሁም የመረጃ ወቅታዊነትና ትክክለኛነትን ማሳደግ አገልግሎቱ ከዩኒሴፍ ጋር በጋራ ከሰራቸው በዋነኝነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ አስረድተዋል።

እነዚህም ተግባራት የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

በቀጣይም በጋራ በሚሰሩባቸውና ድጋፍ በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፤ በዋናው ግቢ የሚገኙ መጋዘኖችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

#ማገልገል_ክብር_ነው!
ማኅሌት አበራ
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service