የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ፣ከክልል ጤና ቢሮ ፣ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር የአገልግሎቱን ተሰብሳቢ ሂሳብ አመላለስ፤ የሂሳብ አያያዝና የኦዲት ሂደት እንዲሁም የ2019 ዓ.ም የበጀት ዕቅድን አስመልክቶ ውይይትና አቅጣጫ ተቀምጧል።
ተቋማት ተሰብሳቢ ሂሳብ በወቅቱ መዝጋት ካልቻሉ አገልግሎቱ በመደበኛ መሠረታዊ መድኃኒቶች የመግዛት አቅሙ ላይ ተፅእኖ እንደሚፈጥር አንስተዋል።
በዚህም ጤና ተቋማት ተሰብሳቢ ሂሳባቸውን በገቡት ውል መሰረት ማጠናቀቅ እንዳለባቸው አሳስበው ፤ የበጀት መዝጊያ ወቅት በመሆኑ ቅርንጫፎች ዕድሉን በመጠቀም የተሻለ ተሰብሳቢ ወደ አገልግሎቱ ገቢ ማድረግ እንደሚገባቸው አቶ ታሪኩ ተናግረዋል።
አክለውም የክልል ጤና ቢሮዎች ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ በማድረግ ተቋማት ተሰብሳቢያቸውን እንዲዘጉ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#ማገልገል ክብር ነው!