በተጨማሪም የአቅርቦት ሥርዓቱ ችግሮችና ፍላጎቶች ለውሳኔ ሰጪዎች በአግባቡ እንዲቀርቡና የሥርዓቱን መሻሻል ለማስፈጸም ድጋፍና ተገቢ ግፊት (Advocacy) መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።
የአቅርቦት ፍሰቱን ለማሻሻል ቁልፍ የፓሊሲ ማሻሻያ እየተካሄደ እንደሆነ የገለፁት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ፤ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ማረጋገጥ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል።
በተያያዘም በዉላቸዉ መሰረት አበረታች ዉጤት ካስመዘገቡ ክልሎች ተሞክሮ በመዉሰድ እና የተረጋጋ ገበያን በመፍጠር የአቅርቦት ስርዓቱን ማሻሻል እንደሚቻል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የግምገማው ተሳታፊዎች ውል የተገባለት የአቅርቦት ሰርዓት /Committd Demand & Supply System (CDSS) /አፈጻጸምን በመገምገም የተገኙ ጥንካሬዎችንና ክፍተቶችን ለይተው በማስቀመጥ፣ ከግምገማው የተገኙ ትምህርቶችን በመጠቀም በቀጣዩ የበጀት ዓመት ለማኅበረሰቡ በቂ የሆነ የሕክምና ግብዓት ለማቅረብ በትጋት እንደሚሠሩ አስታውቀዋል።
#ማገልገል ክብር ነዉ