Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦትን ያሻሻለው ውል የተገባለት የአቅርቦት ሰርዓት  "CDSS" ዓመታዊ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
July 07, 2026
264 views

የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦትን ያሻሻለው ውል የተገባለት የአቅርቦት ሰርዓት "CDSS" ዓመታዊ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በግምገማ መድረኩ ላይ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የCDSS ግብረኃይል አባላት፣ የአገልግሎቱ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች፣ የክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊዎችና የፋርማሲ ዳይሬክተሮች፣ እንዲሁም የፌዴራል ሆስፒታሎች ከፍተኛ ኃላፊዎችና የፋርማሲ ክፍል ዳይሬክተሮች ተሳትፈዋል።

በመድረኩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ ከአገሪቱ 5,023 የሕዝብ ጤና ተቋማት መካከል 4,961ዱ (98.7%) ውል በመፈረም የሥርዓቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ ስኬት ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የአቅርቦት ሥርዓት ለመዘርጋት የCDSS ትግበራ ወሳኝ ሚና እንዳለው ያሳየ መሆኑንም አክለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ በበጀት ዓመቱ የ24.2 ቢሊዮን ብር ፍላጎት ተሰብስቦ 567 መሠረታዊ የሕክምና ዓይነቶች (line items) ሥራ ላይ እንዲውሉ መደረጉን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በጤና ሚኒስቴር የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች መሪ ሥራ አስኪያጅ አቶ ረጋሳ ባይሳ፤ የ2018 ዓ.ም. ክንውንን መነሻ በማድረግ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ በጋራና በቅንጅት መሥራት የታየው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። በቀጣዩ ዓመት ይበልጥ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የፌዴራል እና የክልል ጤና ቢሮዎች የCDSS ዝርዝር ክንውኖቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ አገር አቀፍ አጠቃላይ ሪፖርቱ ቀርቦ በከፍተኛ አመራሮች ውይይት ከተደረገበት በኋላ የቀጣይ የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በመጨረሻም የክልል እና የጤና ተቋማት ሀላፊዎች አገልግሎቱ (EPSS) ከላይ እስከታ በመቀናጀት ከመቼው በተሻለ የህክምና ግብአቶችን አቅርቦት በዚህ አመት በመቅረቡ ምስጋና አቅርበዋል ።
#ማገልገል_ክብር_ነው
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service