Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
የ2019 በጀት ዓመት የጤና ፕሮግራም ግብዓቶች የፍላጎት ትንበያና ማረጋገጫ ውይይት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
July 07, 2026
279 views

የ2019 በጀት ዓመት የጤና ፕሮግራም ግብዓቶች የፍላጎት ትንበያና ማረጋገጫ ውይይት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በውይይቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር ድኤታ ወ/ሮ ፍሬሕይወት አበበ እና የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ተገኝተዋል።

በመድረኩ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚሸፍነው ሀገራዊ የጤና ፕሮግራም ግብዓቶች የፍላጎት ትንበያ (Forecast) ውጤት ከበጀት ፍላጎት ጋር ቀርቦ ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠበት ሲሆን፣ ይህ ትንበያ በመላው ሀገሪቱ ለሚገኝ ማኅበረሰብ—በተለይም ለእናቶች፣ ለሕፃናትና ለታካሚዎች—ተመጣጣኝ የጤና አገልግሎት በፍትሐዊነት ለማድረስ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር ድኤታ ወ/ሮ ፍሬሕይወት አበበ በሰጡ
ት አስተያየት፤ የጤና ፕሮግራም ግብዓቶች ምጠና በጥራት መከናወኑ የሕክምና ቁሳቁሶች ከመጠን በላይ ተከማችተው እንዳይባክኑ ወይም የእጥረት ችግር እንዳይከሰት ለመከላከል ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው፣ ይህም ጠንካራ የጤና አቅርቦት ሰንሰለት ለመገንባት መሠረት መሆኑን አስገንዝበዋል።

አክለውም፣ የትንበያው ትክክለኛነት ሊረጋገጥ የሚችለው ከቀጣዩ የአቅርቦት ዕቅድ ጋር ሲተሳሰር ብቻ በመሆኑ፣ ለጋሽና አጋር ድርጅቶች በቅንጅትና በየጊዜው በሚደረግ ክትትል እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው፣ በ2018 በጀት ዓመት ከተጠየቁት የጤና ፕሮግራም ግብዓቶች ውስጥ በከፍተኛ መጠን ማቅረብ መቻሉን አስታውሰዋል። ይህንን ጥንካሬ አቅጣጫ በማድረግም፣ በ2019 በጀት ዓመት ግዥዎችን በወቅቱ ለመፈጸም በፍጥነት ጨረታ እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service