የአፍሪካ የህክምና ግብዓት ማኑፋክቸሪንግ ንግድ፣ ኤግዝቢሽንና ኮንፍረንስ (African Health Manufacturing Trade, Exhibition and Conference- AHMTEC 2026) አዘጋጅ ኮሚቴዎች አገልገሎቱን ጎበኙ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ኢትዮጵያ የ2026 የአፍሪካ ሀገራት የህክምና ግብዓት ማኑፋክቸሪንግ ንግድ፣ ኤግዚቢሽንና ኮንፍረንስ AHMTEC 2026 ከኦክቶበር 6 እስከ 8 የምታዘጋጅ ሲሆን ፤ በዚህም አዘጋጅ ኮሚቴዎች በአገልግሎቱ ጉብኝት አድርገዋል።
በመድኃኒትና የህክምና መገልገያዎች አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ታሪካዊ የሆነው ኤግዚቢሽንና ኮንፍረንስ በ2025 በጋና አክራ የተከናወነ ሲሆን ሀገራችን በዘርፉ የተደረገው ሰፊ ድጋፍና የተመዘገበውን ተስፋ ሰጪ ውጤት ከግምት በማስገባት AHMTEC-2026 እንድታዘጋጅ ልትመረጥ ችላለች።
ይህንን ተከተሎ ከተለያዩ ሀገራትና ተቋማት የተውጣጡ የአዘጋጆች ቡድን ጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የቅድመ ዝግጅት ምልከታና ጉብኝት ላይ ሲሆኑ በአህጉሩ አንጋፋ የሆነው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትም ቡድኑን በደማቅ አቀባበል በመቀበል ዝግጁነቱን አሳይቷል።
አዘጋጅ ኮሚቴዉ በአገልግሎቱ በመገኘት በቅድመ ዝግጅቱ ዙሪያና አጠቃላይ በመድኃኒት አቅርቦቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ፤ የአቅርቦት ሰንሰለት ስትራቴጂዎች እንዲሁም ተቋሙ የፋርማሲዩቲካል አምራች ዘርፉን ለመደገፍ የሄደበት ርቀትና ቀጥይ ስራዎችን በማቅረብ ሰፊ ገለጻ ተደርጎ ውይይት ተከናዉኗል፡፡
ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱ በሀገራች በጤናው ዘርፉ ለአምራች ኢንዱስትሪው የተሰጠውን ትኩረትና የተገኙት መልካም ተሞክሮዎችን ከመቀመርና ማስፋት ባሻገር በአፍሪካ የዘርፉን አህጉራዊ ጥምረት በማጠናከር ጥራትና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጠ መድኃኒቶች ለዜጎች ቀጣይነት ባለው ዓግባብ ለማቅረብ ያነገብነውን ተልእኮ እውን ለማድረግ የማይተካ ሚና እንደሚኖረው የአገልግሎቱ ም/ዋ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ተናግረዋል።
የመድኃኒት እና መገልገያ መሳሪያዎች አምራች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሰ ተፈሪ እንደተናገሩት ኤግዚብሽኑ እንደ ሀገር አቅማችንን እና በፖሊሲ ረገድ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለአፍሪካዊያን እና ለዓለም ለማሳየት ፤ ለአምራቾች የገበያ ትስስርን ለመፍጠር እንዲሁም ወደ ኢትዮጵያ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በኤግዚብሽን እና ጉባኤዉ በዋናነት ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት እንዲሁም ሌሎች አለም አቀፍ አምራቾች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ!
ሰላም ይደግ