በመስክ ምልከታው ወቅት ከኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት (EQA) የተውጣጣው የግምገማ ቡድን በተቋሙ በመገኘት የEPSSን የሥራ አፈጻጸም እና የጥራት አመራር ሥርዓት በተለያዩ ዘርፎች በጥልቀት ገምግሟል።
ቡድኑ በተለይም የጥራት አስተዳደር ሥርዓት፣ የአመራር አፈጻጸም፣ የሰው ሀብትና ፋይናንስ አስተዳደር፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የሕክምና ግብዓት መጋዘኖች አያያዝና የተገልጋዮች እርካታ የተመለከቱ የሥራ አፈጻጸሞችን መገምገሙ ተገልጿል።
የመስክ ምልከታው በEPSS የሚተገበሩ የጥራት ማሻሻያ ሥርዓቶችን፣ የሥራ ሂደቶችን እና የተገልጋይ ተኮር አገልግሎትን በመመዘን ተቋሙ አሰራሩን ከምርጥ ተሞክሮዎች ጋር በተሻለ ሁኔታ እንዲያጣጥም የሚያግዝ ጠቃሚ የግብረመልስና የማሻሻያ መድረክ እንደሚሆን ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የጥራት ባህልን በማጠናከር፣ የሥራ ቅልጥፍናን በማሻሻልና የተገልጋዮችን እርካታ በማሳደግ ለሀገራዊ የመድኃኒት አቅርቦት ሥርዓት የላቀ አስተዋጽኦ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
#ማገልገል_ክብር_ነው!