Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
ተስፋን እንትከል አገልግሎቱ ከ20 ሺህ በላይ ችግኞችን ተከለ
News
August 14, 2026
171 views

ተስፋን እንትከል አገልግሎቱ ከ20 ሺህ በላይ ችግኞችን ተከለ

በሸገር ከተማ ገፈርሳ ጉጄ በተካሄደው መርሃ ግብር የEPSS ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ የማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አገልግሎቱ ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የራሱን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገልጸው፣ በተለይም የመድኃኒትነት ይዘት ያላቸው ዕፅዋት መተከላቸውን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም EPSS በዚህ ክረምት ተማሪዎችን በትምህርት ቁሳቁስ መደገፍ፣ ማዕድ ማጋራትና የቤት እድሳት በማከናወን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ያቀደ ሲሆን፣ ሰራተኞችም በበጎ ፈቃድ ሥራዎቹ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

#ማገልገል_ክብር_ነው!
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service