ልዑካኑ ከሕክምና ግብዓቶች ግዥ ሂደት ጀምሮ እስከ መጋዘንና ለጤና ተቋማት ቀጥተኛ ስርጭት ድረስ ያለውን የአቅርቦት ሰንሰለት አሰራር ተመልክተዋል።
የEPSS ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ የተቋሙን ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች፣ የአሰራር ሥርዓቶችና የለውጥ ሂደቶች በስፋት አስረድተዋል። በተጨማሪም ልምድ ልውውጡ በአፍሪካ ሀገራት መካከል የእርስ በርስ ትብብርንና የጤና አቅርቦት ሥርዓትን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
አገልግሎቱ በ2030 አሰራሩን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር፣ የመድኃኒቶችን ተገኝነት ለማሳደግና ጥራት ያላቸውን መድኃኒቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ሀገራት ማቅረብ እንዲችል እየሰራ መሆኑን ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጸዋል።
የታንዛኒያ የፕሮግራም ግብዓቶች ኃላፊ ዶ/ር ሼምሳ በበኩላቸው EPSS መድኃኒቶችንና ክትባቶችን በተቀናጀና በተደራጀ ሥርዓት ማስተዳደሩ እንዳስደነቃቸው ገልጸዋል። አገልግሎቱ የሚጠቀመው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እጅግ የላቀ መሆኑን ጠቅሰው፣ በጉብኝቱ በርካታ ልምዶችን ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
በጉብኝቱ ማጠቃለያ ልዑካኑ የEPSS መጋዘኖችን፣ የደህንነትና የኔትወርክ መቆጣጠሪያ ክፍሎችን በመጎብኘት የአሰራር ሂደቶቹን በተግባር ተመልክተዋል።
#ማገልገል_ክብር_ነው