Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በባህር ዳር ዘመናዊ የሕፃናት ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከል አስመረቀ
News
August 14, 2026
200 views

የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በባህር ዳር ዘመናዊ የሕፃናት ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከል አስመረቀ

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታዎች ክብርት ፍሬህይወት አበበ እና ክብርት ሰሀርላ አብዱላሂ፣ የEPSS ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ፣ የሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ዳታ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎችና የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የEPSS ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንደገለጹት፣ የሕፃናት ማቆያ ማዕከሉ ሠራተኞች ልጆቻቸውን በአቅራቢያቸውና በደህንነት እንዲያስቀምጡ በማስቻል በሥራቸው ላይ በተሻለ ትኩረትና እፎይታ እንዲሠሩ ያግዛል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ፕሮጀክቱ ለሴቶች፣ ለሕፃናትና ለቤተሰብ ምቹ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር የተያዘውን የመንግሥት አቅጣጫ በተግባር ያሳየ መሆኑን ገልጸው፣ ለባህር ዳር ቅርንጫፍ ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ መጠናቀቂያ እንግዶች በቅርንጫፉ ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በማከናወን ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።

በሌላ በኩል፣ የEPSS ባህር ዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አምሳሉ ጫኔ እንደገለጹት፣ ቅርንጫፉ በበጀት ዓመቱ የ7.8 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን መድኃኒቶችና የሕክምና ግብዓቶችን ለጤና ተቋማት አሰራጭቷል።

ሥራ አስኪያጁ ለዚህ ውጤት ከዋናው መሥሪያ ቤትና ከአጋር ድርጅቶች የተደረገውን ድጋፍ በማድነቅ፣ ለክብር እንግዶችና ለማዕከሉ ግንባታ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

#ማገልገል_ክብር_ነው
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service