Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
የ3 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዱን በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር እየሠራ ነው
News
August 14, 2026
377 views

የ3 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዱን በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር እየሠራ ነው

የመድረኩ ዋና ዓላማ የEPSS የ3 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድን ከፌዴራል የጤና ዘርፍ የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ጋር ማጣጣም እና በሁሉም የሥራ ክፍሎችና በ19ኙም ቅርንጫፎች የሚተገበሩ የሥራ ዕቅዶችን በማዘጋጀት ወደ ሙሉ ትግበራ ማሸጋገር ነው።

ዕቅዱ የመድኃኒት ግዥና አቅርቦት፣ የመጋዘንና ስርጭት ሥርዓት፣ የፋይናንስ ጤናማነት፣ ዲጂታል ሽግግር፣ የሰው ኃይል ልማት፣ የአደጋ ሥጋት አስተዳደር፣ ክትትልና ግምገማ፣ ተገዢነትና ኦዲትን የሚያጠናክሩ 9 ስትራቴጂክ ግቦችና 64 ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያዎች (KPIs) ያካተተ ነው።

በሁለተኛው የመድኃኒት አቅራቢ ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ (PSDIP II) መሠረትም ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ከፍተኛ በጀት መመደቡ ተገልጿል። በጀቱም የመጋዘን፣ የትዕዛዝ አስተዳደርና የስርጭት ሥርዓትን ለማጠናከር እንዲሁም ወደ ዲጂታል የአቅርቦት ሰንሰለት ለማሸጋገር እንደሚውል ተጠቁሟል።

የዕቅዱ ዋና ትኩረቶች የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ፣ የፋይናንስ ዘላቂነትን ማረጋገጥ፣ ተለዋዋጭና አስተማማኝ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት መገንባት እና ከፍተኛ አፈጻጸም ያለው የሰው ኃይል ማፍራት ናቸው።

ዕቅዱ በየደረጃው በውይይት የዳበረ በመሆኑ፣ የመድኃኒት አቅርቦት ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ፣ የዕቅድ ቅንጅትን (Alignment) በማረጋገጥ እና ለተግባራዊነቱ በጋራ በመረባረብ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ ተገልጿል።

የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፅጋቡ ገብሩ እንዳስገነዘቡት፣ ሁሉም የሥራ ሂደቶችና ቅርንጫፎች በተካሄደው የሥራ ማሳያ መድረክ መሠረት ዕቅዱን አካተው መሥራት ይገባቸዋል። በቀጣይም የዕቅዱን አፈጻጸም ለማረጋገጥ ጥብቅ ክትትልና ግምገማ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

EPSS በ2030 በአፍሪካ ብቁ፣ ቀልጣፋና ፈጣን ምላሽ ሰጪ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ድርጅት የመሆን ራዕዩን ለማሳካት የስትራቴጂክ ዕቅዱን በተቀናጀና በቁርጠኝነት ለመተግበር እየሠራ ይገኛል።

#ማገልገል_ክብር_ነው
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service