የምዘናው ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ከሁሉም ቅርንጫፎች ሠራተኞች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ (Town Hall Meeting) በተደረገ ውይይት ተካሂዷል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፣ ምዘናው በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለመገምገም፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመር፣ ክፍተቶችን ለመለየት እና የሪፖርቶችን ተጨባጭነት ለማረጋገጥ ዕድል ፈጥሯል።
አገልግሎቱ ከባለፈው ዓመት አንጻር የተሻለ የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦት አፈጻጸም ማስመዝገቡን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይህም የመላው ሠራተኞች የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
ቅርንጫፎች ለማኅበረሰቡ መሠረታዊ መድኃኒቶችንና የሕክምና ግብዓቶችን የሚያደርሱ ዋና ማዕከላት በመሆናቸው፣ ተልዕኳቸውን በብቃት መወጣት ለጤና ሥርዓቱ መጠናከር ወሳኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በ2019 በጀት ዓመት በምዘናው የተለዩ ክፍተቶችን በማረም፣ የዲጂታል አሠራሮችን በማጠናከር እና የተሻሉ ተሞክሮዎችን በማስፋት የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።
ላለፉት አራት ቀናት በተካሄደው የቅርንጫፎች የአፈጻጸም ግምገማ ከ60 በላይ ገምጋሚዎች ተሳትፈዋል። በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ዙሪያ ያተኮሩ 100 የመመዘኛ ቼክሊስት መጠይቆችም ተዘጋጅተው በጋራ መግባባት የምዘና ሂደቱ ተጠናቋል።
#ማገልገል_ክብር_ነው