ኢትዮጵያ የክትባት አስተዳደርን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ሀገር አቀፍ ጥናት ተጀመረ።
News
January 26, 2026
95 views

ኢትዮጵያ የክትባት አስተዳደርን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ሀገር አቀፍ ጥናት ተጀመረ።

ኢትዮጵያ የክትባት አስተዳደርን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ሀገር አቀፍ ጥናት ተጀመረ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሀገሪቱን የቀጥታ የክትባት ስርጭት 62% እና የጤና ፕሮግራሞች የቀጥታ ስርጭት 75% እንደሚያሰራጭ ይታወቃል ፤ በመሆኑም የተቀናጀ ውጤታማ የክትባት አስተዳደር ፣ የክትባት ብክለት ቁጥጥር እና የሙቀት መጠን ክትትል ጥናት በኢትዮጵያ ለመስራት የማስጀመሪያ ስነስርዓት በአገልግሎቱ ግቢ ተካሂዷል ።

ኢትዮጵያ ለበርካታ አመታት መከላከል ላይ ያተኮረ የጤና ፖሊሲ ይዛ እየሰራች እንደምትገኝ በዚህም ጠንካራ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ያነሱት በጤና ሚኒስቴር የክትባት አገልግሎት ሀላፊ አቶ መልካሙ አያሌው ፤ በዚህም የጤና ፖሊሲውን ከሚያስቀጥሉት ተግባራት መካከል የምንሰጠው ክትባት ጥራቱን ጠብቆ እየተሰራጨ እንደሚገኝ መከታተል ሲሆን ይህንንም በዚህ ጥናት ለማረጋገጥ ያግዘናል ብለዋል ።

ለጥናቱ በዋነኝነት ከGAV ለጋሽ ድርጅት ድጋፉን መገኘቱን አቶ መልካሙ ተናግረው ሌሎች አጋር ድርጅቶ አስተባብሮ ወደ ተግባር በመግባቱን OPN አመስግነዋል ።

ይህንን ጥናት ከማንም ተፅዕኖ ነፃ ሆናችሁ መስራት ይገባል ብለው ያሳሰቡት ሀላፊው ፤ ጥናቱ የተሳካ እንዲሆን የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናደርጋለን ብለዋል ።

የአገልግሎቱ የ78 አመታት ተቋሚዊ ጉዞ እና ስትራቴጂክ እቅድ የአገልግሎቱ ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ያቀረቡ ሲሆን ፤ ጥናቱ በ2030 እንደ ተቋም የያዝነውን ግብ ለማሳካት ፣ አሁን ምን ላይ እንደደረስንና ማስተካከል ያሉብንን ጉዳዮች በጉልህ እንደሚያሳየን ትልቅ ተስፋ ይጣልበታል ሲሉ አቶ ሰለሞን ገልፀዋል ።

በዚህ ጥናት የሚሰራው አዲስ ነገር ምን ምን እንደሆነ ፣ ጥናቱ የሚዘጋጅበትን ዝርዝር ፣ መረጃ ለሚሰበስቡ አካላት ስልጠና መሰጠቱን እነዚህንና ሌሎች ጉዳዮችን የስራ ሂደት አማካሪ እና ጥናት አስተባባሪ አቶ ወንድወሰን በዝርዝር አቅርበው ፤ ጥናቱ የቅርብ ጊዜ መረጃ እንዲኖር እንደሚያደርግና WHO በሚጠይቀው መሰረት ሪፖርተር ማዘጋጀት እንደሚያስችል አስረድተዋል ።

# ማገልገል ክብር ነዉ!
ዘጋቢ ማኅሌት አበራ
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service