በጉብኝታቸው ወቅት የኢመአአ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ አገልግሎቱ በኢትዮጵያ የመድኃኒትና የጤና ግብዓቶች ግዥ፣ አቅርቦት፣ ማከማቻና ስርጭት ዘርፍ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ለልዑካኑ ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል።
በተጨማሪም የአገልግሎቱን የግዥ፣ የማከማቻና የስርጭት ሥርዓት፣ እንዲሁም ለጤና ተቋማት የሚደረገውን የመድኃኒትና የጤና ግብዓት አቅርቦት በተመለከተ መረጃ ቀርቦላቸዋል።
የጃፓን የፓርላማ አባላቱ በተለይም በመድኃኒት አቅርቦት ዘርፍ የኢመአአን ሚና፣ የአቅርቦት ሥርዓቱን አሠራር እና በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ሥራዎችን ተመልክተዋል።
ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ በኢትዮጵያና ጃፓን መካከል በጤና፣ በመድኃኒት አቅርቦትና በጤና ግብዓቶች ዙሪያ ያለው ትብብር ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑን ገልጸው፣ ጉብኝቱ በመድኃኒት አቅርቦት ዙሪያ ያለውን የልምድና የቴክኒክ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
በጉብኝታቸው መጨረሻም የፓርላማ አባላቱ የአገልግሎቱን መጋዘኖች፣ የደህንነት እና የኔትወርክ መቆጣጠሪያ ክፍሎችን በመዘዋወር ተመልክተዋል።
#ማገልገል_ክብር_ነው