በጉብኝቱ ወቅት ተሳታፊዎቹ የተቋሙን የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ግዥ፣ አቅርቦት፣ ማከማቻና ስርጭት ሥርዓት ተመልክተዋል። በተጨማሪም በቴክኖሎጂ የታገዙ የቁጥጥር፣ የክትትልና የአስተዳደር ሥርዓቶችን በተመለከተ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ሚስተር መሐመድ አሊ Djibouti Secretary General of the Ministry of Health በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የተቋሙን የሕክምና ግብዓቶችን በሚያሰራጭበት ወቅት የሚጠቀመው የቁጥጥር ሥርዓት በጣም አስደንቋቸዋል። በጉብኝቱ ያገኙትን ልምድ በመውሰድ በጅቡቲ ተመሳሳይ አሠራር ለመተግበር ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል።
አፍሪካ የመድኃኒት ፍላጎቷን በራሷ አቅም ለመሸፈን የያዘችውን ዓላማ ለማሳካት ኢትዮጵያ በጤና ግብዓት አቅርቦት ሰንሰለት ዘርፍ እያከናወነች ያለው ሥራ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው አቶ መሐመድ አሊ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የፋርማሲ ተቋማት ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ተረፈ፣ የተቋሙን መጋዘኖች የውስጥ አሠራር በቴክኖሎጂ የታገዘ መሆኑና የተዘረጋው አጠቃላይ የቁጥጥር ሥርዓት እንዳስገረማቸው ገልጸዋል።
አቶ አለማየሁ አክለውም፣ አገልግሎቱ መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ በማቅረብ ለኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት ጠንካራ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ባገኙት ልምድ በመነሳት በየአገራቸው የጤና ግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ሥርዓትን ለማሻሻል የሚያግዙ ተሞክሮዎችን ለመውሰድ ዕድል አግኝተዋል።
ጉብኝቱ በምስራቅ አፍሪካ የጤና ግብዓት አቅርቦትን ለማጠናከር፣ ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥ እንዲሁም በአገራት መካከል ያለውን የጤና ዘርፍ ትብብር ለማስፋት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሯል።
#ማገልገል_ክብር_ነው