ይህ ዓለም አቀፍ እውቅና አገልግሎቱ በመድኃኒትና በሕክምና ግብዓቶች ግዥ፣ በአቅርቦት ሰንሰለት አመራር እና በአሠራር ቅልጥፍና ያሳየውን የላቀ አፈጻጸም የሚያረጋግጥ እውቅና ነው።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የተገኘው ሽልማት አገልግሎቱ በአቅርቦት ሰንሰለት ዘርፍ እያከናወነ ላለው የለውጥና የማሻሻያ ሥራ አስፈላጊ ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም የዲጂታል ሽግግር፣ በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ አሰጣጥ፣ የግዥ ሂደቶችን ማሻሻልና ማጠናከር እንዲሁም የአቅርቦት ሰንሰለቱን ውጤታማነት ማሳደግ ለዚህ እውቅና መገኘት የጎላ ሚና እንደነበራቸው ዋና ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።
ዶ/ር አብዱልቃድር እንደገለጹት፣ የተገኘው እውቅና አገልግሎቱ በ2030 በአፍሪካ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ምላሽ ሰጪ የመድኃኒት አቅርቦት ተቋም ለመሆን የያዘውን ራዕይ ለማሳካት አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምድ ነው።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ይህ ሽልማት የአመራሩና የሠራተኞች የጋራ ጥረት፣ ትጋትና ቁርጠኝነት ውጤት መሆኑን ገልጸው፣ ለሕብረተሰቡ የተሻለ፣ የተረጋጋና ተደራሽ የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓት አቅርቦትን ለማረጋገጥ ሥራው በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ማገልገል ክብር ነው!