Active Tenders
3
ET-MOH-526522-GO-RFB ICB
Closes: 23 Dec 2026
36 days remaining
ET-MOH-537673-GO-RFB ICB
Closes: 10 Dec 2026
23 days remaining
ET-MOH-527291-GO-RFB ICB
Closes: 06 Oct 2026
Closed 42 days ago
View All
የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎችን አቅርቦት ለማሻሻል   የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ጤና እንክብካቤ ፌዴሬሽን ታሪካዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
News
September 01, 2026
343 views

የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎችን አቅርቦት ለማሻሻል የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ጤና እንክብካቤ ፌዴሬሽን ታሪካዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

የስምምነቱ ዋና ዓላማ ከግል የጤና ዘርፍ የሚመጣውን የመሠረታዊና ሕይወት አድን መድኃኒቶች፣ እንዲሁም የሕክምና መገልገያዎች ፍላጎት በአንድ ላይ በማሰባሰብ የግዥ አቅምን ማሳደግ፣ የተሻለ አቅርቦት ማረጋገጥ እና ተደራሽነትን ማሻሻል ነው።

የኢትዮጵያ ጤና እንክብካቤ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ እንደገለጹት፣ ይህ አጋርነት የEPSSን የግዥና የአቅርቦት ሰንሰለት አቅም በመጠቀም የመድኃኒት አቅርቦትን ለማሻሻል፣ ዋጋን ተመጣጣኝ ለማድረግ እና አስተማማኝ አቅርቦትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

ዶ/ር ማርቆስ አክለውም፣ ስምምነቱ በቅድሚያ ከፍተኛ ትኩረት በሚሹ ምርቶች ላይ በማተኮር ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብና ከትግበራው በሚገኘው ትምህርት መሠረት አቅምን በተራ ደረጃ እያጠናከሩ ለመሄድ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ “የግል ወይም የመንግሥት ታካሚ የሚባል የለም፤ ያለው ጥራት፣ ተመጣጣኝ ዋጋ የሚፈልግና አስተማማኝ የጤና አገልግሎትን የሚሻ አንድ ታካሚ ብቻ ነው” ብለዋል።

አጋርነቱ በተለይም የማደንዘዣ (Anesthesia)፣ የካንሰር ሕክምና (Oncology) መድኃኒቶች እና የዲያሊሲስ (Dialysis) መገልገያዎችን ፍላጎት በአንድ ላይ በማሰባሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እና የገበያውን መረጋጋት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጸዋል።

የትብብር ስምምነቱ የጤና ዘርፍን ከEPSS የግዥና የአቅርቦት ሰንሰለት አቅም ጋር በማጣመር የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ተደራሽነትን፣ ተመጣጣኝነትን እና አስተማማኝነትን በማሳደግ ለተሻለ የጤና አገልግሎት አቅርቦት የሚያበረክት መሆኑ ተገልጿል።
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service