ሀገር ውስጥ ምርት ለጤናው ዘርፍ፡ አገልግሎቱ ከአምራቾች ጋር የነበረውን አፈጻጸም ገመገመ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እ.ኤ.አ በ2030 በአፍሪካ ፈጣንና ቀልጣፋ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ያለው ተቋም ለመሆን የያዘውን ራዕይ ለማሳካት እየሰራ ይገኛል።
ይህንኑ ግብ ለማሳካት የሀገር ውስጥ አምራቾችን አቅም ማሳደግና ተሳትፏቸውን ማጠናከር አንዱ ቁልፍ ስትራቴጂ ነው።
በዚሁ መሰረት፣ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ከሀገር ውስጥ አምራቾች ጋር የአፈጻጸም ግምገማ አካሂደዋል።
በውይይቱ ላይ አምራቾች የህክምና ግብዓቶችን በተሰጣቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማቅረባቸውና ያልቀረቡ ግብዓቶች በሚጠናቀቁበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በግምገማው ወቅት ዋና ዳይሬክተሩ የሚከተሉትን ዋና ዋና የአሰራር አቅጣጫዎች ሰጥተዋል፦
✅ብክነትን መቀነስ፦ በመጋዘን በቂ ክምችት ያላቸው የህክምና ግብዓቶች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው (Expiry date) እንዳያልፍ ለማድረግ፣ አምራቾች የማምረቻ ጊዜያቸውን እንዲያዘገዩ ተደርጓል።
✅አቅርቦትን ማፋጠን፦ በክምችት እጥረት ያለባቸው ግብዓቶች በአጭር ጊዜ ተመርተው ለአገልግሎቱ እንዲቀርቡ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ይህ እርምጃ በመድኃኒት አቅርቦት ላይ የሚታየውን መቆራረጥ ከመቅረፉ ባለፈ፣ ያለአግባብ የሚባክኑ የህክምና ግብዓቶችን ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ይጠበቃል።
#ማገልገል_ክብር_ነዉ!