የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ የአዋጅ ቁጥር 1354/2017 ትግበራ ያለበት ደረጃ ገመገመ።
News
January 26, 2026
134 views

የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ የአዋጅ ቁጥር 1354/2017 ትግበራ ያለበት ደረጃ ገመገመ።

የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ የአዋጅ ቁጥር 1354/2017 ትግበራ ያለበት ደረጃ ገመገመ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አዲሱን የማቋቋሚያ አዋጅ ተከትሎ እያከናወናቸው ያሉ የሪፎርም ስራዎችንና ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በዝርዝር ገመገመ።

ቁልፍ የለውጥ ነጥቦች እና የሪፎርም ስራዎች የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ወርቀሰሞ ማሞ እና ምክትል ሰብሳቢው ዶ/ር ታደለ ቦርቃ በተገኙበት በተካሄደው በዚህ ግምገማ፤ ተቋሙ የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማዘመንና የመድኃኒት እጥረትን በዘላቂነት ለመቅረፍ የጀመራቸው ስራዎች ውጤታማ መሆናቸው ተመልክቷል።

በግምገማው ወቅት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንደገለጹት፤ አዋጁን መሠረት በማድረግ የሚከተሉት ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች ተወስደዋል፦

✅ዲጂታላይዜሽን (Smart Digital Health Supply Chain) የተቋሙን አሰራር ዘመናዊና ግልጽ ለማድረግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ በጥሩ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል።

✅የመሠረተ ልማት ዝመና፡ የመድኃኒት መጋዘኖችን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ (Standardized) ለማድረግ ሰፊ የሪፎርም ስራዎች ተከናውነዋል።
አዲሱ አዋጅ ተቋሙ ተወዳዳሪና ቀልጣፋ እንዲሆን ትልቅ ዕድል ፈጥሯል፤ ከፍተኛ አመራሩ እያደረገ ያለው ክትትልና ድጋፍ ለተመዘገበው ስኬት መሰረት ነው — ወ/ሮ ወርቀሰሞ ማሞ (የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ)
የመስክ ምልከታ እና ቀጣይ አቅጣጫ
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በተቋሙ መጋዘኖች ተገኝተው የተከናወኑ የዲጂታላይዜሽን እና የንብረት አያያዝ ስራዎችን በአካል ተመልክተዋል።

አባላቱ በሰጡት አስተያየት፤ ተቋሙ የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙን በማሳደግ የፈጠረው ለውጥ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው፣ የህዝብን የጤና ዋስትና ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ኮሚቴው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ማገልገል ክብር ነው!
ሠላም ይደግ
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service