በርክክቡ ሥነ ሥርዓት ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የእንግሊዝ መንግሥት ላደረጋቸው ወቅታዊ ድጋፎች አመስግነዋል።
ልገሳው ድንበር አቋርጠው የሚመጡ በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን ለመዋጋት እና የጤና ተቋማት ለሕዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ የመስጠት አቅምን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተናግረዋል።
ዶ/ር መቅደስ አክለውም የተለገሱት መሣሪያዎች በወረርሽኝ ምላሽ ጥረቶች ውስጥ የተሳተፉ ግንባር ቀደም የጤና ባለሙያዎችን ለመጠበቅ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ ተናግረዋል።
የዩኬ አምባሳደር ዳረን ዌልች እንዳሉት ዩናይትድ ኪንግደም ኢትዮጵያ የሕክምና መሳሪያዎችን በማምረት ረገድ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ትደግፋለች።
የሁለቱ ሃገራት ትብብር ከኢትዮጵያ አልፎ ለአህጉራዊ እና ለዓለም አቀፍ የጤና ደህንነት አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል።
አምባሳደሩ ጠንካራ የጤና ሥርዓቶች ድንበር ተሻጋሪ አደጋዎችን የሚፈጥሩ ወረርሽኞችን ለመከላከል እና ለመቋቋም አስፈላጊ መሆናቸውን አፅንዖት ሰጥተዋል።
ድጋፉ የግል መከላከያ መሳሪያዎችን (PPE) እና ወሳኝ የምርመራ ኪቶችን ያካተተ ሲሆን፣ ይህም የኢትዮጵያን የወረርሽኝ መከላከል ዝግጁነት እና ምላሽ ለማሻሻል እንደሚያግዝ ተገልጿል።
# ማገልገል ክብር ነዉ!